የፍቅር እንባ

176

በሰርጉ ግብዣ ላይ ጭንቃችንን አይታ
ወደልጇ ሄደች አልቆየችም ፋታ
ወይን ጠጅ እኮ አልቋል ጋኑም ባዶነው
ባለችውም ጊዜ ውሃውን ለወጠው

የፍቅር እንባ /2/
እናት አለችን ሁሌ የምታነባ

ዛሬም እናታችን ጭንቃችንን አይታ
ፊቷን አታዞርም አትሔድም ታክታ
በልጇ ፊት ቆማ እንባዋን እያዘራች
ወይን የላቸውም እያለች ትላለች

ሰዎች በመታበይ ፍቅርሽን ሲክዱ
የፍቅር እንባሽን በመርገጥ ሲሄዱ
ያንቺ እንባ ለእነሱ አሁንም ይፈሳል
ስለነሱ ልብሽ በፍቅር ይነዳል

ልጇ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ እያየች
የፍቅር እንባዋን እጅግ አፈሰሰች
አዛኚቱ እናቱን ለእኛ ሰጥቶናል
የፍቅር እባዋም ስለኛ ይፈሳል

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top