የመልአኩን ቃል

176

የመልአኩን ቃል እንዳልከው ይሁን በማለትሽ

ከዙፋኑ ወርዶ ወደ እግ/ር ጌታ ኢየሱስ
ወዳንቺ መጣ መረጠሽ ቅዱስ መንፈስ
ከሴቶች ሁሉ ንፅት ሆነሽ ስለተገኘሽ
በማህፀንሽ አደረ ጌታ አንቺ ብርቱ ነሽ

ያልታሰበ ስጦታ ሰጠን የፍጥረት ጌታ
ሥጋሽን ለብሶ ለአንቺ ሆነሽ የርሱ ስጦታ
ምስጋና ይድረስሽ እንልሻለን እኛ ሁላችን
በአንቺ ምክንያት ስለታደሰ መላ ሕይወታች

የህይዋን እዳ በአንቺ ተካስ እመቤታችን
የገነት ደጅ አስከፋቻችን አስታራቂያችን
መመኪያችን ነሽ አለኝታ ነሽ ድንግል ማርያም
ጌታን አቅፈሽው የሚኖረው ከላይ ከአርያም

ለዚህ የታደልሽ የምህረት እናት አማላጃችን
ምላሽ ሁኚልን የሕይወት መሰላል መዳኛችን

አይጨክን ሆድሽ ርህሩህ እናት ባንቺ ተማምነን
በረድኤትሽ እንዳትለይን እንልሻለን

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top