ያለው ይሆናል

-

እግዚአብሔር ያለው ይሆናል
ሰው መልከመልኩ ሁሌ ይዳክራል
የእርሱ ሃሳብ ሁሉ ይፈፀማል
የፈቀደው ይከናወናል

ያለው ይሆናል አሃ አሃ
ጌታ ያለው ይሆናል
ይከናወናል አሃ አሃ
እርሱ ካለ ይሆናል

1. እኔ ጉልበት አንዳችን ላልጨምርም
ከፀጉሬ እንኳን አንዷን ላልቀይርም
እንዲያው ስሮጥ ምንም ላይተርፈኝ
የሚያስገባኝን አገኘሁኝ

ይኸው ዛሬ ግን ጌታ ሲጐበኘኝ
ለጥያቄዬ ሁሉ መልስ አዘጋጀልኝ
እርሱ ባለው ቀን ጌታ ባቀደልኝ
ለእንቆቅልሼ ሁሉ መልስ አገኘሁኝ

ያለው ይሆናል አሃ አሃ
ጌታ ያለው ይሆናል
ይከናወናል አሃ አሃ
እርሱ ካለ ይሆናል /2/

2. ያለው ላይቀር ሲደርስ ሰዓቱ
በራስ ሃሳብ ላይ ታች ማለቱ
ላይሞላልኝ ጊዜን መፍጀቱ
የሚለፋት እንዲያው በከንቱ

ጌታ ባለው ቀን ፈቅዶ ሲወስን
ቀድሞ ያቀድኩት ሁሉ አየሁ ሲፈፀም
ምንም ቢዘገይም ለኔ ባይመስልም
ጌታ ያከናውናል በእርሱ አላፍርም

ሆኖ አይተናል አሃ አሃ
ጌታ አድርጐ አየተናል
ይከናወናል አሃ አሃ
ጌታ ካለ ይሆናል /2/

ያለው ይሆናል አሃ አሃ
ጌታ ያለው ይሆናል
ይከናወናል አሃ አሃ
እርሱ ካለ ይሆናል /2/

የምስጋና

Leave a Comment

Scroll to Top