ያብቃ የሽንገላ ዘመን

129

ያብቃ የሽንገላ ዘመን ከዓለም ጋር
ወንድሜ/እህቴ/ አትታለል/ይ/
ላትቆይ በምድር ላይ ሺህ ዓመት
ይሻላል ብታደርገው ተወት

ላያዛልቅህ ሕይወት ከዓለም ጋር ጨዋታ
…..ዋ!
ዘመኑ አብቅቶ አንድ ቀን ሲገታ
ዋስትና የሌለው ጊዜ እንደ ጥላ ነው
…..ዋ!
ቋሚ አስተማማኝ ኢየሱስ ብቻ ነው

በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን እወቅ
…..ዋ!
በዓለም ውጣ ውረድ ጉልበትህ አይላቅ
ውለታን ለማያውቅ ለዓለም አትልፋ
…..ዋ!
ወስን ሁሉን ትተህ ጌታ ይሁን ተስፋህ

ዛሬ በሚታየው ፈፅሞ አትመካ
…..ዋ!
የመኖር ዋስትናህ በዚህ አትለካ
እስከ ዘለዓለም ፀንቶ የሚኖረው
…..ዋ!
ማንም ምንም የለም ኢየሱስ ብቻ ነው

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top