ዓይኔ እንዳላየ ጆሮዬ እንዳልሰማ /2/
እንዴት እንዴት ልሁን እኔ አልችልም
አፌም ለውለታህ ዝም አይልም /2/
ዕለት በዕለት ድንቅ እያሳየኝ
ጌታ አድራጎትህ ስላስገረመኝ
ደግሞ ላውራ እንጂ ለመጪው ትውልድ
እንዴት መልሼ ይህን ልካድ /2/
አንዴም አላውቅም ርቄ ከቤትህ
ከድንቄ ሥራ ከታምራትህ
አምኖ ዓይኔ አይቶ ጆሮዬም ሰምቶ
አልችልም መኖር ይህን እረስቶ
ይህን ዘንግቶ
ማውራት አንዳይችል ነፍስ እንደሌለው
እንደቁም ባሕር ዝም እንደሚለው
ይቅርብኝ እኔስ እንዲህ መኖር
አብቅቶኝ የሱስ ለቁም ነገር
ለዚህ ክብር
ያልነበርኩትን ዛሬ ሆኛለሁ
አዲስ ነው ስሜ አዲስ ሆኛለሁ
ባንተ ነው የሱስ ይህ የሆነልኝ
ሁሉም እውነት ነው ምስክርህ ነኝ /2/
