ጌጤ ሃብቴ ነህ

76

ጌጤ ሀብቴ ነህ ትልቅ ቅርሴ
ገበና ጓዳ ልዩ ኢየሱሴ
በችግር ድካም ያለህ ከጐኔ
አለኝታዬ ነህ አለኝታዬ

ለዚህ ከንቱ አለም ተጋለጥኩ እኔ
በኃጥያት ተንኮል ተጋርዶ አይኔ
ብቻዬን ስባዝን በሃዘን አለንጋ
አሁን ግን መጣሁ አንተን ፍለጋ
መሻሉን አወኩ ንሮ ከአንተጋ

ለእኔ ሁሉም ነህ የምኮራብህ
የአንጀቴን ሚስጥር የማማክርህ
በምድር በሰማይ አንተ ልዩ ነህ
ማነው ሚደርስህ ሚወዳደርህ
በሕይወቴ ውስጥ ልዩ ስፍራ አለህ

ስሙን ጠርቼ ከጭንቅ አርፋለሁ
ምንም ቢመጣ በእርሱ እመካለሁ
ከዘንዶ ከአውሬ ይጠብቀኛል
ሁሌ ነቅቶ ነው ይጠብቀኛል

የኔ አለኝታ ምሽግ ሆኖኛል

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top