ፍቅርህን አልብሰን

41

ፍቅርህን አልብሰን ጌታ እንድንተሳሰብ
መንፈስ ቅዱስ ገብቶ ይስራ በእያንዳንዳችን ልብ
ልባችንን ለእርሱ ከፍተን ጌታን እንለምን
በሰላም በደስታ በፍቅር በቸር እንዲሞላን

1. እንደራስህ ውደድ ሌላውን ሰው ሁሉ
ብሎ ያስተማረን የአምላካችን ቃሉ
ከመሐከላችን ጠፍቶ እውነትና ፍቅር
በኛ ላይ ነገሰ ጥልና ክርክር /2/

ፍቅርህን አልብሰን ጌታ እንድንተሳሰብ
መንፈስ ቅዱስ ገብቶ ይስራ በእያንዳንዳችን ልብ
ልባችንን ለእርሱ ከፍተን ጌታን እንለምን
በሰላም በደስታ በፍቅር በቸር እንዲሞላን

2. በጦርነት በርሀብ በስደት መከራ
የሰው ልጅ ይኖራል እንባውን ሲዘራ
ረዳት እንደሌው ከዘመድ ከስጋ
ሲንከራተት ያድራል መጠጊያ ፍለጋ /2/

ፍቅርህን አልብሰን ጌታ እንድንተሳሰብ
መንፈስ ቅዱስ ገብቶ ይስራ በእያንዳንዳችን ልብ
ልባችንን ለእርሱ ከፍተን ጌታን እንለምን
በሰላም በደስታ በፍቅር በቸር እንዲሞላን

3. ሁሉ እንዳይቀርብን ሌት ተቀን ስንለምን
ለበደለን እንኳን ይቅርታ አላደረግን
በአምላክ አምሳያ የተፈጠረውን
እንዴት ዘነጋነው ሰው ክቡር መሆኑን /2/

ፍቅርህን አልብሰን ጌታ እንድንተሳሰብ
መንፈስ ቅዱስ ገብቶ ይስራ በእያንዳንዳችን ልብ
ልባችንን ለእርሱ ከፍተን ጌታን እንለምን
በሰላም በደስታ በፍቅር በቸር እንዲሞላን

4. አንዳንዱ በረሐብ ተሰቃይቶ ሲሞት
ሌላው ተቸግሮ ይኖራል በስደት
አይናችን እያየ የሰውን መከራ
በዝምታ አንለፍ ልባችን ይራራ /2/

ፍቅርህን አልብሰን ጌታ እንድንተሳሰብ
መንፈስ ቅዱስ ገብቶ ይስራ በእያንዳንዳችን ልብ
ልባችንን ለእርሱ ከፍተን ጌታን እንለምን
በሰላም በደስታ በፍቅር በቸር እንዲሞላን

5. ቸርነትህ ብዙ ምህረትህ ዘላለም
ምንጊዜም ለጋስ ነህ ፍቅርህ ከቶ አያልቅም
እንለምንሀለን በምትወደው ልጅህ
ፍቅርህን ላክልን ምንም አይሳንህ

ፍቅርህን አልብሰን ጌታ እንድንተሳሰብ
መንፈስ ቅዱስ ገብቶ ይስራ በእያንዳንዳችን ልብ
ልባችንን ለእርሱ ከፍተን ጌታን እንለምን
በሰላም በደስታ በፍቅር በቸር እንዲሞላን

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top