ይቅር በለን አምላክ በደምህ እጠበን
ንስሐ ገብተናል ያንተ መሆን ፈልገን
ጌታ ይቅር በለን ምሕረት አድርግልን
ኮብልለን እንዳንጠፋ ጌታ ሆይ ከቤትህ
አብቃን ለንስሐ ከኛ ይራቅ ኃጢያት
በፃድቃን ተጋድሎ በሰማዕታት ደም
አድለን በረከት ፍቅርና ሰላም
ይህ ዓለም ጠፊ ነው በሃብት አትመኩ
ሥጋውንና ደሙን አምነን ከተቀበልን
መተውም አለብን ቂምና በቀልን
መቀበል በድፍረት ሳይተው ቂም በቀልን
እያዩ መግባት ነው ከሚያቃጥል እሳት
ሥጋውን ከበላን ደሙንም ከጠጣን
ዘላለማዊ ሕይወት ሁልጊዜ አለን
መዳኛ ብቻ ነው ሥጋውና ደሙ
ኢየሱስ ክርስቶስ ቸሩ መድኃኒዓለም
ብሎናል ጌታችን ተስፋችሁን እንኩ
ሰጥቶናል ጌታችን ሥጋውና ደሙን
ቀሪ ዘመናችን ሊባርክ ጌታችን
ከኃጢያት ነጽቶ ያልተቀበለ ሰው
