እነሆ የዋህ በግ
የታረደልን ለህግ
እወነተኛው መስዋእት
ኑ እንስገድለት
በእውነት አባታችን
መልካም እረኛችን
ደጉ ወዳጃችን
ነህ መዳኛችን
ሥጋና ደምህን
በውነት ሰጠኸን
የህይወት ምንጫችን
ምግብ ለነፍሳችን
የነፍሴ ቃልኪዳን
እንዳልረሳህ አንተን
ጻፍልኝ መዝገብህን
በልቤም ፀጋህን
ለሰማይ ለምድር
የሚያስጨንቅ ሚስጥር
ይኖራል በመንበር
ልንበላው ዘወትር
የፍቅር እሳት
የሕይወት መብራት
በዚያች ቀን ሰአት
ነፍሴን አድናት
