ንጉሥ ነኝም ብሎ በሥልጣኑ አልኮራ
በአህያ የሚቀመጥ ትሁት የሚራራ
የተናቀውንም ደግሞ አከበረን
ለመንግስቱ ሾመን ካህናት አደረገን
ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ምስጋና
ሆሳዕና ትሁት ንጉሥ ነውና
ሆሳዕና ይገባዋል ምስጋና /2/
አሜን
ፊታችሁ ወዳለችው ከተማ ሂዱና
ሰው ያልተቀመጠባት ውርንጫ አለችና
ፈታችሁ አምጧት ደግሞ ማንም ቢከራከር
ጌታ ፍልጓታል በሉት እንድትከብር
በተዋረደው እንደውርንጫም በሆነው
ሊቀመጥ ወዷልና ልባችን እንስጠው
ውርንጮችም ነበርን ለሸክም የታጨን
ሸክማችንን ተሸከክሞ ኢየሱስ አከበረን
ነፍሴ ሆይ አትፍሪ እልል እልል ሰይ
የሚያውኩሽ ሁሉ ጠፍተው እንድታይ
ንጉስሽም ትሁት ሆኖ ወደንቺ መጥቷል
ዘንባባ ይዘሽ ዘምሪ በይ እልል
