እልልታ ደመቀ ምድር ተሸበረ
ሁሉም ይዘምራል ሆሳዕና እያለ
ዝም በለ ቢባል እንኳ ማንችሎ ዝም ይላል
አፍ የሌለው ድንጋይ ግዑዝ ይናገራል
ሆሳዕና በሰማይ ሆሳዕና በምድር
ዘንባባ ይነጠፍ ክብር ለእርሱ ይሁን
ክብር ለኢየሱስ /3/ ለገናናው ንጉስ
ምንድነው ሁካታ ምንድነው ሽብሩ
የዘንባባው ንጣፍ ለማነው ክብሩ
የነገስታት ንጉስ የጌቶቹ ጌታ
የናዝሬቱ ኢየሱስ በዚህ ሊያልፍ መጣ
ሆሳዕና በሰማይ ….
እስረኛ ተፈታ ቀንበር ተሰበረ
ዘመን ለእርሱ መጣ ጌታን አከበረ
እንዴት ያስችለዋል አይቶ ታምራቱ
ብዙ ብዙ ነገር ሆኖ በህይወቱ
ሆሳዕና በሰማይ ….
ነፍስም አይቀርላት ሁሉም ያከብረዋል
የእርሱን ታላቅነት ፍጥረት ተረድቶታል
ከፍ ብሎ ይታይ ከማንም በላይ
እርሱ ብቻ ንጉስ በምድር በሰማይ
ሆሳዕና በሰማይ …..
