የተሸለምሽ ድንኳን ነሽ
የእርግብ ክንፍ ምስጋና ይድረስሽ
በወርቅ በብር ያሸበረቅሽ
ከፀሐይ ደምቀሽ ታበሪያለሽ
እፁብ ድንቅ እናት
የምታስደንቅ ታላቅ ሕይወት
የክርስቲያኖች እረዳት
እንዘምር እንወድሳት
ከተራሮች ከፍ አልሽ
ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ
ከከበሩት ከበርሽ
ምስጋና ይድረስሽ በመንበርሽ
የአጥቢያ የብርሐን እናት
ሰውን ወዳድ የሁሉ እመቤት
ማደሪያ ሆንሽ ለእግዚኣብሔር
አይገኝልሽም ወደር
ፍፁም ትሁት የሆንሽ
የጲላጦስ እንጨት ደስ ይበልሽ
ድንግል እናት በመሆንሽ
የአለሙን ጌታ ተሸከምሽ
