ማደሪያ ለትሆኚ ለአለሙ ንጉስ
እናት ልትሆኚ የተመረጥሽ ለክርስቶስ
መቃጠል ያልነካሽ ነዲድ እፀጳጦስ
ሂዋንን ያሳተ ምቀኛ ዲያቢሎስ
ሰይጣን የአዳም ጠላት እባቡ አፈረ
በእግርሽ ተረገጠ ናላው ተሰበረ
መልኩ ተለወጠ ድራጐን ሆነ ዘንዶ
በእግርሽ ተረገጠ እገሀነም ወርዶ
ማርያም እመቤቴ አዛኝ እረዳቴ
አማልጅኝ ስደክም ሁሌ በውድቀቴ
ስላንቺ ወደሴ ስለአንቺ ሰለምታ
ምላሴ ላንቂዬ ይሁን የተፈታ
አመፅ የሚደፍር ጌታን ከማይፈራ
አድኚን ጠብቂን ማርያም ሆይ አደራ
ግፍን አንደ ሱስ ልቡን ካላመደው
ሰውሪን አደራ ሐጥያት ከማይከብደው
ከሰይጣን አድኚን ሰወሪን ከክፋ
ፈጣሪን ከረሱ ጠፍተው ከሚያልፋ
