ዘወትር ከፊትሽ

179

ሠላም ለአንቺ ይሁን ቅድስት ማርያም
ስምሽ ይባረክ እስከ ዘለአለም
የአሸናፊ እናት ክብር ይድረስሽ
ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ ነሽ

ዘወትር ከፊትሽ እቆማለሁ
ፀሎቴን እንድትሰሚኝ አምናለሁ
የሚሳነው የለም ለልጅሽ
አማልጅን ቅድስት ሆይ እባክሽ

ማርያም ሆይ አንቺ ፀጋ ተሞልተሻል
ከፍጥረት አልፎ ጌታ አንቺን መርጦሻል
የማህፀንሽ ፍሬ የተባረከ ነው
ሐያሉ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው

የሰው ዘር ሁሉ ስምሽን ይጥራ
ክብርሽ በአለም እንዲያበራ
ከኛ ጋር ሁኚ የሰላም ንግስት
በሞት ጐዳና ሆነ በህይወት

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top