ፀጋ የሞላሽ ማርያም
እግዚአብሔር የመረጠሽ ከአርያም
በእውነት ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ ነሽ
የሆድሽም ፍሬ ተባርኳል ልጅሽ /2/
1. የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን ብለሽ
ማርያም ባለውለታ /2/
መዳንን አመጣሽ ታዛዥ ሆነሽ
ማርያም ባለውለታ /2/
ተጠጋገነ የአለም ስብራት
እኛም ተፈታን ከጭንቅ እስራት
ባዘጋጀሽው ራስሽን ለኣስራት
ብርሃን ወጣልን በኢየሱስ መምጣት
ማርያም ባለውለታ /3/
ውለሻል ታላቅ ውለታ /3/
ፀጋ የሞላሽ ማርያም
እግዚአብሔር የመረጠሽ ከአርያም
በእውነት ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ ነሽ
የሆድሽም ፍሬ ተባርኳል ልጅሽ /2/
2. በበረሃ በግብፅ ደግሞም በቤተልሔም
ማርያም ባለውለታ /2/
ቢሰለፍ መከራ አላቆመሽ ይኼም
ማርያም ባለውለታ/2/
ተከናወነ የንጉስ መምጣት
በምጥ ላይ ላለው ሆነለተ ብስራት
ተከናወነ የንጉስ መምጣት
ሊያበቃለት የሰይጣን ግዛት
ማርያም ባለውለታ /3/
ውለሻል ታላቅ ውለታ /3/
ፀጋ የሞላሽ ማርያም
እግዚአብሔር የመረጠሽ ከአርያም
በእውነት ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ ነሽ
የሆድሽም ፍሬ ተባርኳል ልጅሽ /2/
