ዝቅተኛይቱ የእግዚአብሔር አገልጋይ
ማርያም በፊቱ የእግዚአብሔር አገልጋይ
ዛሬ ከእርሱ ያለሽ በሰማይ
ፍፁም አስተማሪ ህይወትን ኖረሽ
እንዲህ ይነገራል ስራሽ
የህይወት ገድልሽ ታዛዥነትሽ
ስራሽ ገድልሽ መልካሙ ንሮሽ
ለልደቱ ቀናው ያ ልብሽ
ለሞቱ ያነባው ያ ፍቅርሽ
አስተማሪው ይሄ ገድልሽ እህህ
ሲወሳ ይኖራል በምድር ላይ
ሕይወት ለካ ይህ ነው የአገልጋይ
እስከመጨረሻው ፀንቶ የሚታይ አሀሀ
በቃሉ ሲመጣ ውዱ ጌታ
በውስጥሽ የሞላው ሁሉ ሽታ
በፍቅር ሲገለጥ በዝቅታ
እግዚአብሔር ከበረ በክብርሽ
ሚስጥሩን ነገረ ለልብሽ
ለሄዋን ታድሶ አረገሽ አሀሀ
