የእመቤቶች እመቤት

213

የእመቤቶች እመቤት
የተለየሽ ልዩ ሴት
ኢየሱስ ሞገስ የሆነሽ
ማርያም ኦ አንቺ ነሽ

ከፍጥረታት ምቹ ጠፍቶ
የጽድቅ እጣው ለአንቺ ወጥቶ
እግዚአብሔር ወልድ መጣልን
የመዳን በር ሊሆነን
ከአንቺ መጥቶ ጌታችን
ተከፈለ እዳችን

የሚታመን በሌለበት
በተስፋ እንኳን ሚጽናኑበት
ይሁን አልሽው ለመላኩ
አንቺው ብቻ ሆንሽው ልኩ
ይሁን አልሽው ለመላኩ
አንቺው ብቻ ሆንሽው ልኩ

ጸደቀና እሽታሽ
ፀጋ ሞላ በውስጥሽ
ለይቶሻል ለእርሱ አለም
ለአምላክሽ ሚሳን የለም

ለይቶሻል ለእሱሱ ዓለም
ለእግዚአብሔር የሚሳን የለም

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top