በቸርነትህ

218

በቸርነትህ አሃ አመታትን ታቀዳጃለህ
በምድር በዳ ስብን ታጠግባለህ
ተራሮችም ሳይቀሩ ይረካሉ
ኮረብቶችም ወደአንተ ይሰግዳሉ አሜን /2/

1. በጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገባል
ሥጋ ለባሽ ሁሉ ክበር ይልሃል
ምድርን በቡቃያ ሞልተህ
ፍጥረትን አስደሰትክ ባርከህ

በቸርነትህ አሃ አመታትን ታቀዳጃለህ
በምድር በዳ ስብን ታጠግባለህ
ተራሮችም ሳይቀሩ ይረካሉ
ኮረብቶችም ወደአንተ ይሰግዳሉ አሜን

2. በሃይልህ ተራሮችን ሁሉ አጽንተሃል
በጥበብ አለምን በድንቅ መርተሃል
ሕዝብህን ከጥፋት ታድገህ
አሁን ያደረስከን አንተ ነህ

በቸርነትህ አሃ አመታትን ታቀዳጃለህ
በምድር በዳ ስብን ታጠግባለህ
ተራሮችም ሳይቀሩ ይረካሉ
ኮረብቶችም ወደአንተ ይሰግዳሉ አሜን

3. ቤተ መቅደስ ገብቶ ብራናው ሲፈታ
የእውነት መንፈስህ በኔ ላይ ነው ሲል ጌታ
የምስራች ቃሉ ታወጀልን
ሕዝቦች ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን

በቸርነትህ አሃ አመታትን ታቀዳጃለህ
በምድር በዳ ስብን ታጠግባለህ
ተራሮችም ሳይቀሩ ይረካሉ
ኮረብቶችም ወደአንተ ይሰግዳሉ አሜን

4. አምላክ ኤልሻዳይ ነው ታግሶናል
በእድሜያችን ላይ ጌታ ዛሬን አክሏል
ከርሱ የሆነልን ስጦታ
ስሙን እንወድሰው በእልልታ

በቸርነትህ አሃ አመታትን ታቀዳጃለህ
በምድር በዳ ስብን ታጠግባለህ
ተራሮችም ሳይቀሩ ይረካሉ
ኮረብቶችም ወደአንተ ይሰግዳሉ አሜን /2/

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top