ከሃና ከእያቄም የተወለደች
ታዛዥቷ ፍጡር የተመረጠች
መድሃኒትን ወልዳ ብርሃን የሆነች
የምዘምርላት የአምላኬ እናት ነች
የጌታዬ እናት ነች የንጉሴ እናት ነች
በደህንነት ዕቅድ ትልቅ ስፍራን ይዛ
ማደሪው የሆነች ለዓለም ቤዛ /3/
መንገድ ለመዳን /3/
የመከራ ጀግና የትዕግስት አብነት
ምሳሌ የእውነት ምሳሌ የእምነት
ለኛም የተረፈች ከፀጋዋ ሙላት
እሷ የኖህ መርከብ መዳኛችን ናት
ያለ አዳም ሀጢያት የተወለደች
ከትውልድ መካከል የተባረከች
በስደት በእሳት የተፈተነች
ያዳነን እየሱስ ንጉስ ወለደች
