ሁሉንም አየሁ

226

ሁሉንም አየሁ አየሁ /2/
ዙሪያዬን አየሁ አየሁ /2/
እንዳንተ መልካም አላገኘሁም
እንዳንተ ወዳጅ አላገኘሁም
እንዳንተ አፍቃሪ አላገኘሁም

አይለዋወጥም ፍቅርህ ጌታ
ሁሌም አዲስ መሽቶ ሲነጋ
አሣርፎኛል ባንተ መታመን
እኖራለሁኝ ያለ ሰቀቀን

ሥላለህ አንተ አጠገቤ
አይፈራም አይሰጋም ልቤ
ቀኖቼ ደስታ ናቸው
ጌታ አንተ የባረካቸው

የክፉ ደራሽ ነህ ጓደኛዬ
የማትለየኝ ከአጠገቤ
ሆነህልኛል ጽኑ አለት
ከስጋት ጭንቀት ማመልጥበት

ትርጉም ነህ ለምኖርበት
በልቤ የምፅናናበት
ሣስብህ ደስታ ይሰጠኛል
ተስፋዬ ሆነህኛል

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top