ይኽው ዛሬ ቀብቶሃል ከሕዝቡ በሃል መርጦሃል
ግልገሎቼን ጠቦቶቼን በጎቼን ጠብቅ ይልሃል
የሙሴን በትር ሰጥቶሃል ሂድ ሕዝቤን ምራ ይልሃል
እንዳትፈራ በበረሃ እነድታጽናናው ይልሃል
እሺ በል ጉዞህን ጀም ለሕዝቡ አንተን መርጦሃል
ውደማወርሳቸው ምድር ይዘሀቸው ሂድ ይልሃል
አንተ ታማኝ አገልጋይ በጌታ ደስ ይበልህ
የምስጋና መዝሙር ዘምር ክብር ስጥ ለአምላክህ
ከተናቅህበትም ስፍራ ከፍ አርጎ ዛሬ መርጦሃል
እንደዳዊት ቀብቶሃል በፊቱም አድኖሀል
መንፈሱን አዝንቦልሃል መልክተኛዩ ብሎሃል
አንተን ዛሬ አንሰቶሃል በዘየቱም ቀብቶሃል
ልጄ ሆይ ምንም አትፍራ ከአንተ ጋራ ነኝ ይልሃል
እኔ ወደ ማዝህ ስፍራ መልክቴን አድርስ ይልሃል
እንደ ስምኦን እንደ ጴጥሮስ እወድሃለሁ ብሎሃል
መስቀሉን ይዘህ ተከተል እርሱ እራሱ ይረዳሃል
ጉዞህን ጀምረሃል ወደ ሌላ አትይ የልሃል
መልክቴን ሳታስተላልፍ እንደ ዮናስ አትሁን ይልሃል
