የቅዱስ ማደሪያ

233

የቅዱስ ማደሪያው ፀጋውን አትረፍርፎ
ነፃ አውጥቶናል ጨለማውንም ገፎ /2/
እነሆ የአምላክ እናት በስምሽ ስንጠራሽ
ወደ ልጅሽ እንድናድግ ደስ ብሎናል በስራሽ /2/

እርሱ የሚለንን አንድናደርገው ሁሉ
እሽታን አስተምሪን እንዲፈጸም የቃሉ /2/
ዓለም እንዲድንበት እንዲሳካ ፍቃድ
እባክሽን አማልጅን ምቹ እንዲሆን መንገዱ /2/

ለብዙዎች መዳን መሰላል ሆነሽናል
የናትነት ፍቅርሽ አንድ ላይ ሰብስቦናል /2/
እንግዲህ ኑ ወገኖች ህብረታችን ይወራ
የፍቅር ጥሪው ገብቶን በውስጣችን እንዲሰራ /2/

ምስጋና ይገባል ለኪዳነምህረት
ልጅዋን ለሰጠችን ለመድሀኒያለም እናት /2/
እናሞግስሻለን ባማረ የድል ዜማ
ላደረግሽው ውለታ ክብር ላንቺ ይሁና /2/

የማርያም
Amharic
St.Gabriel

Leave a Comment

Scroll to Top