በቅዱስ ቁርባን ጠርተኽን
ዛሬ ለዚህ ያበቃኽን
ስጋና ደምህን እንድካፈል ያረከን
የዘላለም ጌታ ሆይ ኢየሱስ የኛ ፈጣሪያችን
በዚህ ክቡር ሚስጥርህ ዘውትር ንገስ
በቅዱስ ቁርባንህ ራስህን የሰጠህ
ፍጥረትን በሙሉ በደምህ የዋጀህ
መና ሆነህ ራስህን ሰጠኽን
እንድናገኝ የዘለአለም ህይወትን
ሰማያዊ ምግብ ሆነህ ከላይ ወረድክልን
ጌታ ሆይ እንደአንተ ማን አዳኝ ይገኛል
በመንበርህ የምትገኝ ትልቅ ሚስጥር ነህ
ተሳትፈን እንድንደርስ አብቃን ለመንግስትህ
ቅዱስ ስጋህና ደምህን ጠጥተን
ወደ ቅዱስ ልብህ እንድንቀርብ አድርገን
ሚስጥርህን አግኝተን ሕይወት እንድናገኝ
ለዘለአለም መንግስትህ በቀኝህ እንድንገኝ
የፍቅር ምግብ ሆነህ ከላይ ወረድክልን
ተቀብለን አንተን ከሞትም እንድንድን
ስጋና ደምህን ወሰድነው በእምነት
ምንቀበለውም ይሁንልን ለህይወት
