ከእናቴ ማህፀን ጀምሮ ያኔ ድሮ
ውለታህ ብዙ አያልቅ ተቆጥሮ
መች ይገልፀዋል የኔ ቃላት በውስጤ ያለው
መግለፅ አልችልም ይከብደኛል ቃላት ያጥረኛል
አቤት አቤት ያንተ ውለታ
አቤት አቤት ያንተ ስጦታ
አቤት አቤት ለኔ ያረከው
አቤት አቤት ብዙ ነው ጌታ /2/
ሲሰማኝ ድካም ሲዝል ጉልበቴ
አይዞህ ስትለኝ ሁሌም በህይወቴ
አልተለየኸኝ አንዴም ለአፍታ
በምን ልግለፀው ያንተን ውለታ ጌታ
ከክፉ ሁሉ ስትከልለኝ
እንደ ዓይን ብሌን ስትጠብቀኝ
በመልካም መንገድ እየመራኸኝ
ደግ እረኛዬ ለዚህ አደረስከኝ
ኧረ እኔ ማን ነኝ
አይገለፅም በቃላት ምጥን
መልካምነትህ በጎነትህ
በቀራንዮ ያሳየኸው
የፍቅር ጥግ መጨረሻው
ኧረ ልዩ ነው ፍቅርህ
