ጌታ ስትመግበን

250

በማሕየዊ በመለኮትህ በሥጋና በደምህ
ሁሌ የምትኖር ጌታችን አንተ ነህ
መድኃኒታችን ሆይ ክብር ስግደት አምልኮ እንስጥህ

ጌታ ስትመግበን መና ከሰማይ
በመንገድ ዝለን እንዳታይ /2/
ፍቅርህን አይተናል ይኸው ያቆመናል
አቤቱ ከማመስገን ሌላ ምን እንበል

ጌታ በበራፍ ቆመህ ልግባ አልክ

የፍቅርን መድረክ እያሰብን /2/
ያንተን ድምፅ ሰምተን በራችንን ከፍተን
እጅግ ደስ የሚያሰኝ ማዕድ እናገኛለን /2/

ጌታ ስታፈስልን ንፁህ ደምህን
በመስቀል ተሰቅለህልን /2/
የቀራንዮ መስዋዕት ሁሌ እያከበርን
እንመሰክራለን የማዳን ስራህን

ጌታ ስትሆንልን የህይወት እንጀራ
እንድንቀርብህ ሳንፈራ /2/
ለዘለዓለም ኖረን ሞትን ድል አድርገን
ህያው እንሆናለን በቃልህ እንደነገርከን /2/

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top