በጨለማ ሳለን ብርሀን አየን
ላዳም ልጆች ሁሉ መዳን ሆነልን
ጌታችን ተወልዶ በቤተልሄም
መዳንን ታወጀ ለዚች አለም
ደስ ይበለን /8/
ቀድሞ በነብያት የተተነበየው
በመልአኩ ገብርኤል እንደተበሰረው
አማኑኤል ተወልዶልናል
ጨለማችን ጠፍቶ ብርሀን በርቶልናል
በከብቶች በረት በቤተልሄም
የነገስታት ንጉስ መድሀኒአለም
ተኝቶ አገኙት እረኞች
ደስታው ተበሰረ ለእኛ ለልጆቹ
ሰባ ሰገል መጡ ህጻኑ ዘንድ
በግርግም አገኙት ከእናቱ ክንድ
እጅ መንሻ አቅርበው ሰገዱለት
ጌትነቱን አውቀው ሊገዙለት
