በብዙ ግርግር ሁካታ ልስማው ያንተን ዝምታ
በብዙ ግርግር ሁካታ ልስማው ያንተን ዝምታ?
ልስማው ያንተን ዝምታ
ምነው ዘግይቼ አንተን ማፍቀሬ
ትናንትናዬ ሊያስቆጨኝ ዛሬ /2/
ቀጥሬህ ልዳን መች እልሃለሁ
የልቤን ጌታ ተረድቻለሁ /2/
ስላንተ እያወቅኩ አንተን አላውቅም
ሥጋን ሳስደስት አንተን አላይም /2/
እውቀት ፍልስፍና የሙጥኝ ይዞኝ
ኢየሱስ ስራህን መቼ አየሁኝ /2/
የሰው ሕይወት በምድር ትግል ነው
የወዝ ደሞዝ እንደሚሻ በሲቃ የተሞላነው
ለፈረሶች ግን ሀይልን የሚስጥ በጋማ የሚያስጌጣቸው
እንዴት እሱ አያውቅ የኔን ተምኔት
ተነስ ብሎ አክብሮ መልስን የሚሰጠኝ
አንድ ያለኝ የምለው ወዳጄ በእውነት ወዳጄ ማረከኝ/2/
