እግዚአብሔር ልጁን ሰጥቶ
ፍቅሩን ገለፀ ለሰው ልጆች
እስከ መስቀል እኛን ወዶናል
ፍቅሩ አለ በውስጣችን
የፍቅር ትርጉሙ ያልገባችሁ
በሚጠፋው ተስፋ ያላችሁ
አስተውሉ እውነት ይህ ነው
እግዚእብሄር እርሱ ፍቅር ነው
ትንቢት ብትናገሩ
ልሳንን ብትደረድሩ
ፍቅር ከሌለ ሁሉም ከንቱ ነው
አትታበዩ ሁሉም ከእርሱ ነው
ፍቅር ታጋሽ ነው አይመቀኝም
ሐሜትን አያውቅ ክፋት አይወድም
ይቅር ይላል ለተበደለው
