እጅግ በጣም ርቃ ከበረሃው መንደር
ብዙ ሰው የያዘች አለች ቅድስት ሀገር
እኔ እናፍቃለሁ ለመኖር /3/ በዚያች ሀገር
የእውነት ከተማ ውሸት የሌለባት
ፅድቅ ቅድስና ክብር የሚገኝባት
ሁከት የሌለባት ሕመምና ችግር
የሰላም ማደርያ መሰረቷ ፍቅር
የሕይወት ዉሃ ነው የፈለቀባት
መላዕክት ቅዱሳን የሚኖሩባት
የማይለዋወጥ ሰላሟ ብዙ ነው
የምገሰግሰው እኔም ወደዚያው ነው
ለዘላለም እረፍት ከአምላኬ እርቄ
በጣም ቸኩያለሁ ለመሄድ ናፍቄ
የሀጢአት እዳዬ ስለተከፈለ
ታዬን ለማየት ሕይወቴ ቸኮለ
ችግሬን አልፌ የዓለምን መከራ
ዘላለም ለመኖር ከጌታዬ ጋራ
ፀሐይ ኢየሱስ ነው የከተማው ብርሃን
በደስታ በሰላም አብረን እንኖራለን
ከበረሃው ማዶ የማያት አርቄ
በጣም ቸኩያለሁ ለመሄድ ናፍቄ
ፊቱን እያየሁኝ እሰግድለታለሁ
ቀንም ቢሆን ሌሊት ሁሌ እዘምራለሁ
