ጌታ እኮ ዝም ያለን

-

ጌታ እኮ ዝም ያለን
እኛ እንዳንጠፋ እንድንድን ነው
ቀን የጨመረልን
በንስሐ ምህረቱን ሊሰጠን ነው /2/

ሃሌ ሉያ /4/

1. ሞኝ ሆኖ አይደለም ዝም ያለን
ስናጠፋ እኛን እያየን
በንስሐ ተመልሰን
እሱ ይጓጓል እኛን ሊያየን

ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር
ከቶ የለም ሁሌ ይላል
ዝም ሲልህና ዘመን ሲሰጥህ
አንተም እንዳትል እግዚአብሔር የታል

ሃሌ ሉያ /4*/

2. እያየ እንዳላየ የሚያልፍህ
ስላልኖረህ አይደል ወይ ስላላየህ
ትላንት አሻግሮ ዛሬን የሰጠህ
ለንስሐ ነው እንዲህ የቆየህ /2/

3. አምናን የለፍከው በእርሱ ነው
ዘንደሮ የለኽው በእርሱ ነው
ይህንን አውቀሀ ማመስገንህ
እውነት ለአንተ ይህ ክብር ነው /2/
ሃሌ ሉያ/4*/

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top