በአንዳች አልጨነቅም

-

1. በአንዳች ነገር አልጨነቅም
የፊቴ ደስታ ከቶ አይጨልምም
የሚያስብልኝ አባት እንዳለኝ አውቃለሁ
የከበደኝን ሁሉ በእርሱ ላይ ተዋለሁ /2/

እኔም እርሱም አስበን አይሆንም ፣
የኔ ጭንቀት ካሳቡ አይበልጥም
እርሱ ይሰማል እኔ ጠይቃለሁ ፣
በእምነት እጄን ዘርግቼ ወስዳለሁ

ሠላም ነው ካንተ ጋር መኖር
ሠላም ነው ካንተ ጋር
እረፍት ነው ካንተ ጋር ጉዞ
ማረፍ ነው ካንተ ጋር

የሚያስጨንቀኝ ጠፋ /2/
ሃሌሉያ /2/ ክብር ለጌታ /2/

2. ምን እበላለሁ ምንስ እጠጣለሁ
ብዬ አላስብም አባቴን አውቃለሁ
ሚያስፈልገኝን አስቀድሞ ያውቃል
መሻቴን አትረፍርፎ ይሠጠኛል /2/

እንደ እርሱ አይነት አባት ኖሮኝ ፣
በምን ልዘን እስቲ ምንስ ጎድሎኝ
በሠማዩም በምድሩም ባርኮኛል ፣
በለምለሙ መስክም ይመራኛል

ሠላም ነው ካንተ ጋር መኖር
ሠላም ነው ካንተ ጋር
እረፍት ነው ካንተ ጋር ጉዞ
ማረፍ ነው ካንተ ጋር

3. በጎ ስጦታ ፍጹም በረከት
ቤቴን ሞልቶታል ሠላምና እረፍት
መልካምነትህን ብቻ ነው የማውቀው
ያልሆነልኝ የለም አመሠግናለሁ /2/

ከግንዱ ጋር ስለ ተጣበኩኝ ፣
ሳላቋርጥ ሁሌ አፈራለሁኝ
ለዘላዓለም ባንተ አርፌአለሁ ፣
ዛሬ ህይወቴን በፀጋህ መኖር ነው

ሠላም ነው ካንተ ጋር መኖር
ሠላም ነው ካንተ ጋር
እረፍት ነው ካንተ ጋር ጉዞ
ማረፍ ነው ካንተ ጋር

ለካ ሰላም አንተ ነህ ለካ ሠላም /2/
ለካ እረፍት አንተ ነህ ለካ እረፍት /2/
ለካ ህይወት አንተ ነህ ለካ ህይወት /2/
በቃ አባት አንተ ነህ ለካ አባት /2/
በቃ ጌታ አንተ ነህ ለካ ጌታ /2/

የምስጋና

Leave a Comment

Scroll to Top