1. በዳዊት ልብ ላመስግንህ – ምሕረትህን አብዛልኝ
ናታንን አትከልክል ከዐይኔ – በደሌን ያንሳ ይገስጸኝ
ልጅህን ዝም አትበለኝ – ስማኝ ከቅዱስ ተራራ
በንሥሐ ፊትህ ልምጣ – ደግፈኝ ልንቃ ሳልፈራ
እረኝነቴን ሳትረሳ – አንተው እረኛዬ ሆነህ
መርተኸኝ በእረፍት ውኃ – በለመለመ መስክ አደርኩ
መች አልሰማኸኝ አንተማ – ዝምታህ /ምርኩዝህ/ አጓጉዞኛል
ፍቅር ነህ ጌታ ተባረክ – ትንሹን እኔን አይተኻል /2/
2. ደዌ ከወገን ለይቶኝ – ተስፋን ያላየሁኝ ዕለት
አንድ ቀን መዋል ይደክማል – እንኳንስ መክረም መሰንበት
ሳልጮህ አየኸኝ እንጂ – እኔማ በየቱ አቅሜ
አዳኝ እጅህ ዳሰሰኝ – ወድቄ አልቀረሁ ደክሜ
እስኪሞላ አልጠብቅም – ላመሰግንህ በቂ ነህ
ያላኖርከኝ መቼ ነው – እስትንፋሴ እኮ አንተው ነህ
ምስጋናዬን ውደድ እንጂ – አልሰማም የጠላት መርዶ
አልፌአለሁ ብዙ ቀን – ዘመን አያስረኝም ከርሞ /2/
3. መና ለዘላለም አይወርድ – ያልፋል ስንዴ ስብ ሲተካው
አዝዕርት አልቆጥር ልሰዋ – ስጦታህ ስፍር አይለካው
ይሽሩን ለዘላለም – አምላክ እንጂ ሚያሳርፈኝ
የድንጋይ ማር ወተት አይደል – መውደድህ እንጂ ሚበቃኝ
ይህ ቁርበቴ ደግሞ ያልፍና – እግዚአብሔር ሆይ አይሃለሁ
የምትቤዠኝ ሆይ ሕያው ነህ – አንተ ብቻ ትጸናለህ
ልቤ አይዝልም በመናፈቅ – አባቴ ዐይኔ አንተን ሲያይ
የምድሩ ከንቱ እንደነበር – በእውነት ፊት በላይ በሰማይ /2/
ላመሰግንህ በቂ ነህ /3/ ላመስግንህ /2/
