ክብርህ ሲታይ በምድር አይቻለሁ
ሞገስህ ቤትህ ሲሞላ ይኸው አሸበሽባለሁ
ምህረትህ ስለበዛ ለእኔ እንኳን
ከዚህም በላይ በሆንኩ ያሰኘኛል /2/
ስራህ ግሩም አስደናቂ
የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ደንቅ አድራጊ
ፍጥረት ሁሉ አንተን ይላል
የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ስምህ ገኗል /2/
ካንተ ሌላ ሰራዬ እንደው ልብ ባይሞላም
ሳላነሳ ብዬ ዝሞ ሌቱ መሽቶ አይነጋ
ስል ተመስገንልኝ አርካታዬ ይበዛል
ለሆንልህ ለክብርህ እጅግ ደስ ይለኛል /2/
እስኪ ዝም ብዬ ልናገር ይኼንን
አምላኬ አንተው ነህ ያኖርከኝ በምድር
አስከ ዘለዓለሞ አመልክሀለሁ
አምላኬ ተመስገን አቀኝልሀለሁ /2/
በምህረትህ ያቆምከኝ
ለዘለዓለም ምትመራኝ
ለጨለማው ብርሃን
ሁሉን ያደረክ አንተው ነህ /2/
አንተው ነህ ጌታዬ አንተው ነህ
አንተው ነህ ኢየሱሴ አንተው ነህ /2/
ኃያል ነህ የኔ ጌታ
ክንደ ብርቱ የማትረታ
ጠላት ቢዘት ቢደነፋ
አይጥለኝም ክብርህ ይስፋ
ሰማይ ምድር በቃልህ
አንተ አይደለህም ወይ ያፀናህ
ሁሉን ማድረግ ትችላለህ
የኔ ጌታ ምን ሊሳንህ
አምላኬ ከፍ ከፍ ብሎአልና
ጌታዬ ከፍ ከፍ ብሎአልና
እየሱሴ ከፍ ከፍ ብሎእልና
አሰዋለሁ ክብር ምስጋና /2/
