ንጉሴን ሾሜዋለው

-

እርሱ ሊልቅ እኔ ላንስ ይገባል
ጌታ ሊልቅ እኔ ላንስ ይገባል
ለልብ አምላክ ሌላ ምን ይሰጣል
በእርሱ ዙፋን እርሱ ይመለካል /2/

በከበረው ተራራ ላይ ንጉሴን ሾሜዋለሁ
ባከበረው ሕይወቴ ላይ ንጉሴን ሾሜዋለሁ
በፍቅር የሚገዛኝ እርሱ ብቻ እግዚአብሔር ነው
ውስጤ ሲማረክለት ልቤን ደስ ደስ አለው /2/

እርሱ ነው ብያለሁ እርሱ ነው
የሕይወቴ የበላይ የምለው
እርሱን ሾሜዋለሁ በላዬ
የፈጠረኝ ሆኗል ምርጫዬ

1. የማይነጥፍ ውሳኔ ነው
እግዚአብሔርን በሌላ አልቀይረው
ይመቸኛል ከእርሱ ጋራ
ይንገሰብኝ ለሌላ የለኝ ስፍራ /2/

ሁሌም ይኼንን ሳዜመው ነው
ወስጤም ሰላም የሚያገኘው /2/

በከበረው ተራራ ላይ ንጉሴን ሾሜዋለሁ
ባከበረው ሕይወቴ ላይ ንጉሴን ሾሜዋለሁ
በፍቅር የሚገዛኝ እርሱ ብቻ እግዚአብሔር ነው
ውስጤ ሲማረክለት ልቤን ደስ ደስ አለው /2/

እርሱ ነው ብያለሁ እርሱ ነው
የሕይወቴ የበላይ የምለው
እርሱን ሾሜዋለሁ በላዬ
የፈጠረኝ ሆኗል ምርጫዬ

2. በፈጠረው ነጻነቴ
ይዘዝበት እግዚአብሔር አባቴ
ደስ ይለኛል ከፍ ብሎ
ሲያስተዳድረ ሲገዛኝ ጠቅልሎ /2/

ሁሌም ይኼንን ሳዜመው ነው
ወስጤም ሰላም የሚያገኘው /2/

በከበረው ተራራ ላይ ንጉሴን ሾሜዋለሁ
ባከበረው ሕይወቴ ላይ ንጉሴን ሾሜዋለሁ
በፍቅር የሚገዛኝ እርሱ ብቻ እግዚአብሔር ነው
ውስጤ ሲማረክለት ልቤን ደስ ደስ አለው /2/

እርሱ ነው ብያለሁ እርሱ ነው
የሕይወቴ የበላይ የምለው
እርሱን ሾሜዋለሁ በላዬ
የፈጠረኝ ሆኗል ምርጫዬ

3. ልጣል በእሳት በማይጠፋው
ሲታይ ሲታይ ውሉ በሚሰፋው
ባያደነኝም አምነዋለሁ
መልቀቅ የለም ንጉሴን ሾሜዋለሁ /2/

ሁሌም ይኼንን ሳዜመው ነው
ወስጤም ሰላም የሚያገኘው /2/

በከበረው ተራራ ላይ ንጉሴን ሾሜዋለሁ
ባከበረው ሕይወቴ ላይ ንጉሴን ሾሜዋለሁ
በፍቅር የሚገዛኝ እርሱ ብቻ እግዚአብሔር ነው
ውስጤ ሲማረክለት ልቤን ደስ ደስ አለው /2/

እርሱ ነው ብያለሁ እርሱ ነው
የሕይወቴ የበላይ የምለው
እርሱን ሾሜዋለሁ በላዬ
የፈጠረኝ ሆኗል ምርጫዬ

የትንሳኤ
Amharic
St.Gabriel

Leave a Comment

Scroll to Top