የቃሉ ማደሪያ

-

የቃሉ ማደሪያ መንበረ ታቦታቸን
የፍቅር መገለጥ የመዳን ተስፋችን
ከጨለማው ዓለም የመውጫ በራችን
ብርሃን ተገለጠ በአመቤታቸን

1. የሕይወታቸን ጉዞ አቅጣጫ ምሳሌ
የእምነት የጽናት የመታዘዝ
የፍቅር ማደሪያ የመዳንም ጽላት
ባንቺ ተቀረጸ መንገድና አውነት

የቃሉ ማደሪያ መንበረ ታቦታቸን
የፍቅር መገለጥ የመዳን ተስፋችን
ከጨለማው ዓለም የመውጫ በራችን
ብርሃን ተገለጠ በአመቤታቸን

2. አስራኤል አምቢ አለች ከአምላኳ ሸፈተቸ
ነቢያት መላእክትን አልቀበል አለች
ስለዚህ እግዚአብሔር ቃሉን አስታወስ
ከምድር ፍጥረታት ንጽሕት ፈለገ

የቃሉ ማደሪያ መንበረ ታቦታቸን
የፍቅር መገለጥ የመዳን ተስፋችን
ከጨለማው ዓለም የመውጫ በራችን
ብርሃን ተገለጠ በአመቤታቸን

3. እንደኛ ኃጢአት ሳይሆን አንደምሕረቱ
ሊያስገቢን ወደደ ወደ ፍቅር ቤቱ
በማርያም አደረ ሰው ሆኖ ሊገለጥ
ክቡር እንደሆንን ሊገልጽ ሊያረጋግጥ

የቃሉ ማደሪያ መንበረ ታቦታቸን
የፍቅር መገለጥ የመዳን ተስፋችን
ከጨለማው ዓለም የመውጫ በራችን
ብርሃን ተገለጠ በአመቤታቸን

4. እነሆ እስካሁን እናስብሻለን
አውነትን ስለ ያዝሽ አናከብርሻለን
አስከ ቀራንዮ ጸንተሽ በመጓዝሽ
የሕይወታቸን ጉዞ አርአያ አደረግንሽ

የቃሉ ማደሪያ መንበረ ታቦታቸን
የፍቅር መገለጥ የመዳን ተስፋችን
ከጨለማው ዓለም የመውጫ በራችን
ብርሃን ተገለጠ በአመቤታቸን

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top