የገሊላ ሴቶች ተከተሉት
እንባቸውን እዘሩ ለሱ ግርፋት
ያንን ድንቅ ታሪክ ዜናውን አብስሩ
መከራቸውስ ምንድነው ሚስጥሩ
ጎልጎታ ጉዞ ታሪኩን ንገሩን
ጌታ በሕማሙ የመከራችሁን
የቀራኔው ሰምኦን መስቀሉን የያዘ
ይምጣና ይመስክር ጌታውን ያገዘ
ሰሎሜና ማርያም በግልፅ ይናገሩ
ክርስቶስ ሲሰቀል በዚያ የነበሩ
በጉዞ ላይ ሳላ መስቀል ተሸክሞ
በወደቀ ጊዜ እጅግ በጣም ደክሞ
በለቅሶ በዋይታ ወደርሱ ስትቀርቡ
ምን አድርጉ አለ ገነት እንድትገቡ
የኢየሱስ ዘመዶች እናንተ ወዳጆች
በቀራኒዮ መንገድ እንባ ያነባችሁ
ከአምላካችሁ ጋር በሰማይ ያላችሁ
የጎልጎታ ጎዞ ምስክሮች ናችሁ
ታምሜ ደክሜ የጠየቃችሁኝ
በችግሬ ጊዜ ያልተለያችሁኝ
ስለተዘጋጀ በሰማይ ቤት ቦታ
ግቡ ተደስቱ ያላንዳች ቅሬታ
መንግስትን ውረሱ ብሎ የሚጠራቸው
የጎልጎታ ጉዞ ምስክሮች ናቸው
