ከከተማችሁ ወጣ ብላችሁ

9

ለእኛስ ቤዛችን ይህ አይደለም
የምናርፍበት ለዘለአለም
ጌታ በተስፋ የሰጠን
ፅዮን ናት ለኛ መኖሪያችን

ከከተማችሁ ወጣ ብላችሁ
ስትካፈሉ መከራውን የጌታችሁን

የመስቀሉን ፍቅር እናስብ
ጌታ ለኛ የገለፀውን
አዲሱን ኪዳን የከፈተውን
እንካፈል የጌታን መከራውን

የሐዘን ሰይፍ የወጋት እናቱ
ፀንታለችና እስከሞቱ
ከሃዘኗ እንካፈላት
ማርያምን ዛሬ እናግዛት

በምድራዊ ቤት አትታመን
ተስፋህን በጌታ ፀጋ አቁም
እረፍትህ በኢየሱስ ይሁን
በመንፈስ ጥላ ስር መኖር

የልደት

Leave a Comment

Scroll to Top