እልል እንበልለት

21

እልል/3/ እንበል ምስጋናን እንስጠው
መቃብሩን ፈነቃቅሎ ሞትን ድል ለነሳው
መቃብሩን ፈነቃቅሎ በክብር ላረገው

ደስ ብሎናል ዛሬ በጌታ ኢየሱስ
ተነስቷል በክብር ሕይወታችንን ሊያድስ
መለከት ይነፋ እልል እንበልለት
ጉልበቶችም ሁሉ ወድቀው ይስገዱለት

የነበረ ያለ የሚኖር ዘላለም

በኃጢያት ስንጠፋ አይቶ ዝም አላለም
ከሰማይ ሰማያት ከዙፋኑ ወርዶ
አዳነን ልጆቹን በመስቀል ተዋርዶ

ብርሃን አግኝተናል በአብ የበኩር ልጅ
የራሱን ድንቅ ሥራ ጥበቡን እናውጅ
ኃያል ድንቅ አምላክ ነው ሞትን ድል የነሳ
የዓለም ሁሉ ብርሃን የአይሁድ አንበሳ

ለታላቅ ትንሳኤው ሁላችን እንዘምር
እንሰዋ ምስጋና ለእርሱ እንስጠው ክብር
ሕይወት ኣግኝተናል በእርሱ የስቃይ ሞት
እልል እልል እልል እልል እንበልለት

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top