ልመናዬን ሰማኝ የሰማዩ አምላኬ
ነግሬው ነበረ ከምር ተንበርክኬ
ሰው አይቶ የማይንቅ ከአመድ የሚያነሳ
መልካም አባት አለኝ ሁሉን የማይረሳ
ሃያ ሰላሳ አመት በአልጋ ላይ ወድቄ
ሰው ሊያየኝ ሲጠላኝ በበሽታ አልቄ /2/
በምህረትህ እጅህ አንተ ብትዳስሰኝ /2/
ቆሜ ልሄድ በቃሁ ይኸው ወግ ደረሰኝ /2/
ተወግሬ ልሞት ሞቴን ስጠባበቅ
በጨካኝ መዳፍ እንደትቢያ ልደቅ /2/
ምህረት አረክልኝ አንተ መጣህና /2/
እኔም መኖር ጀመርኩ ይኸው እንደገና /2/
ወደር የሌለው ፈጣን ነው ምህረቱ
ለጭንቀት ይደርሳል ኢየሱስ በሰአቱ
ተነሽ ሂጂ አለኝ ፈታኝ ከእስራቱ /2/
ከሞት ጥላ አዳነኝ ደርሶ በሕይወቴ /2/
አላሳፈረኝም ፀሎቴን ሰምቶኛል
ሸክሜን አውርዶ እረፍትን ሰጥቶኛል/2/
ላረገው ውለታ ምን እከፍለዋለሁ [2]
እኔም በአንደበቴ ይመስገን እላለሁ /2/
