ጌታ ሆይ ስማኝ

31

አቤቱ ፀሎቴን ወዳንተ አቀርባለሁ
ችግሬን ጭንቀቴን ይዤ ቀርቢያለሁ
ስለዚህ አምላኬ እርዳታን እሻለሁ
እንደምትሰማኝ እተማመናለሁ

የህይወቴ ሚስጥር አልገባ እያለኝ
ህሊናዬን ከብዶት ዘወትር ሲያስጨንቀኝ
ስጋዬ ሊገዛ መንፈሴን ታከተኝ
ከከበበኝ ፅልመት እግዚአብሔር ሆይ አውጣኝ

የኑሮዬ ዘመን በጣሙን አጠረ
ውጥኔም ምኞቴም መና ሆኖ ቀረ
እንግዲህ አቤቱ ምህረትን እንዳገኝ
እውነት ተከትሎ መኖር አስተምረኝ

ከስደቴ ብዛት በጣሙን ከብዶኛል
ከሀዘን የተነሳ ሞት እኔን ቀርቦኛል
መሐሪ ኣምላክ ሆይ ባሪያህን ታደገኝ

ከዘለአለም ሞት አደራ ጠብቀኝ

እባክህ ሐዘኔን ፍፁም ደስታ አርገው
የጥንቱን ትካዜ ዛሬውኑ ለውጠው
የምስጋና መዝሙር ሁሌ አቀርባለሁ
እስከ ዘለአለሙ አመሰግናለሁ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top