ማራናታ

34

እንዲሁ አንደሄድኩኝ እንዲሁ እመለሳለሁ
ብሎ የተናገረው ኢየሱስ ታማኝ ነው
እኔ እጠብቀዋለሁ ጌታዬ ታማኝ ነው
ማራናታ /4/ ጌታ ሆይ ና /2/

የምድር ውጣ ውረድ ህይወት
አብቅቶ ሁሉም የሚያርፍበት
ማየትን እጅግ እናፍቃለሁ
በእምነት አንተን እጠብቃለሁ /2/

የጦር ወሬ በምድር ሲሰማ
መናወጥም ሲሆን በከተማ
የምፅአት አንዱ ምልክት ነው
የምድር ፍፃሜ ቅርብ ነው በደጅህ ነው

እረፍት ነው መኖር ከአንተጋራ
በአለህበትም በዚያ ውብ ስፍራ
ከመላእክቶች ጋር በአንድነት
አንተን ብቻ ሁሌ የማመልክበት/2/

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top