ትቀድሳት ብዬ ሕይወቴን
ትሞላልኝ ብዬ ምኞቴን
ከእግሮችህ በታች ዝቅ ልጅህ ብያለሁ
አንተን እሻለሁ የሱስ እናፍቃለሁ
እጠብቃለሁ
ሆዴን ከፍቼ ለሰው መንገሬ
ላላገኝበት ቁም ነገር ፍሬ
የመንፈስ ዕረፍት ለኔ አይሰጠኝም
ለጥያቄዬ መልስ አይሆነኝም
ዛሬም እጆቼን ወዳንተ ላቅና}
ለእንቆቅልሼ ሁሉ መልስ አለህና} /2/
በፊትህ መቅረብ ለኔ ያዋጣኛል
ለስብራቴ ፈውስ ይሆነኛል
ጠጋግነኝና ጌታ አሳርፈኝ
ደስታን በውስጤ ኣንተ ኣፍስስልኝ
በዚያ እኖራለሁ ፀንቼ ባንተ }
እኖራለሁኝ ጌታ ኑሮዬን ባንተ} /2/
ያላንተ ማንን ብዬ ልጠጋ
ለውስጥ ሕይወቴ መድን ፍለጋ
ፈውስ ሊሆነኝ ማንም አልቻለም
ሰላም ዕረፍቴ በፍጹም የለም
በፊትህ አለሁ እዳሰስ ብዬ }
በፈውስ እጆችህ ራርተህ ዳሰኝ ጌታዬ } /2/
አካሌ ዛላ ደካክሜያለሁ
ዕረፍት ለማግኘት ብዙ እሮጣለሁ
እፎይ ማለትን አላገኘሁም
ቢመረምረው ሊቅ አይፈታውም
የሱስ ያድናል ሲሉ ሰምቼ }
ተንበረከኩኝ ላንተ ሩጫዬን ትቼ } /2/
ባንተ ታምኜ ሕይወት ዘርቼ
ስላም እፎይታን ካንተ አግኝቼ
ቀልድ ቀርቶብኝ ማፌዜን ትቼ
የሚገባኝን ላንተ ሰርቼ
ዳገቱን መውጣት ቁልቁለት መውረድ
ምንም ኃይል አይኑር ጌታ እኔን የሚያግድ
ለክብርህ ቆሜ እራሴን ላዋርድ }
አንተ አዘጋጀኝ የሱስ በጎቼን ላግድ} /2/
