ማረኝ ማረኝ ጌታዬ/2/
ማረኝ ማረኝ ኢየሱስ /2/
1. ታምራትን ሁሉ እረስቼ
አምላኬ ሆይ ከአንተ ተለይቼ
ሄድኩኝ ወደ ጥፋት ጐዳና
ቀመስኩት ማረኝ ጌታዬ ነህና
ማረኝ ማረኝ ጌታዬ
ማረኝ ማረኝ ኢየሱስ /2/
2. የሰጠኸኝን ማስተዋል ጥዬ
አለምን ሁሉ ተከትዬ
በፊትህ አስቀየምኩህ በሐጥያቴ
ማረኝ አባቴ መጣሁ እጄን ዘርግቼ
ማረኝ ማረኝ ጌታዬ
ማረኝ ማረኝ ኢየሱስ /2/
3. ማስተዋል ሁሉ የታል ስትላኝ
አምላክ ሆይ የምመልሰው ያጣሁኝ
ተከራታቹ ባሪያህ እኔ ነኝ
አምላኬ ባክህ ይቅር በለኝ
ማረኝ ማረኝ ጌታዬ
ማረኝ ማረኝ ኢየሱስ /2/
4. አባት ሆይ ወደአንተ መጣሁኝ
ውዳቂውን ይቅር እንድትለኝ
ጌታ ሆይ ምህረትህ አያልቅምና
እግዚአብሔር ሆይ ማረኝ እንደገና
ማረኝ ማረኝ ጌታዬ
ማረኝ ማረኝ ኢየሱስ /2/
