መንገዴን እንዳልስት

55

መንገዴን እንዳልስት ጌታዬ ሆይ
በትዕግስት ልጠብቅ አባቴ ሆይ /2/
ለሥጋዬ ምቾት ጌታ ሆይ
ጉዞዬን እንዳልተው ጠብቀኝ
ከጉያህ እንዳልወጣ ደጋግፈህ ያዘኝ

1. እውነተኛ ፅድቅን
የምጠማ ልሁን ዘወትር በፊትህ
ትንሹን ፈተና ወድቄ እንዳላሳዝንህ
ውድቀቴን ለሚሻ ጠላቴም አትስጠኝ
በድል አክሊልህን እንድቀበል ዕርዳኝ
በድል አክሊልህን ለመቀበል አብቃኝ

መንገዴን እንዳልስት ጌታዬ ሆይ
በትዕግስት ልጠብቅ አባቴ ሆይ /2/
ለሥጋዬ ምቾት ጌታ ሆይ
ጉዞዬን እንዳልተው ጠብቀኝ
ከጉያህ እንዳልወጣ ደጋግፈህ ያዘኝ

2. ዕረፍት የሚያሳጣ
በሽታ ቢከበኝ ቁስሌ ቢጠና
ፈውሴ ቢዘገይም ለመልካም ፈቃድህ ነውና
መባዘኔን ሽረህ እባክህ አሳርፈኝ
ከመጠበቂያዬ እንዳልጠፋ ዕርዳኝ
ወዲህ ወዲያ እንዳልል እምነት ጨምርልኝ

መንገዴን እንዳልስት ጌታዬ ሆይ
በትዕግስት ልጠብቅ አባቴ ሆይ /2/
ለሥጋዬ ምቾት ጌታ ሆይ
ጉዞዬን እንዳልተው ጠብቀኝ
ከጉያህ እንዳልወጣ ደጋግፈህ ያዘኝ

3. ምድራዊ ምኞቴ
ለምድር ነው እንጂ አይጠቅምም ለሰማይ
ሁሌም ቁልቁል እንጂ አያስኬድም በከፍታው ላይ
ሃሳቤ ካሳብህ ሁሌ እንዲቀራረብ
የፅናትህ መንፈስ በእኔ ላይ ይደረብ /2/

መንገዴን እንዳልስት ጌታዬ ሆይ
በትዕግስት ልጠብቅ አባቴ ሆይ /2/
ለሥጋዬ ምቾት ጌታ ሆይ
ጉዞዬን እንዳልተው ጠብቀኝ
ከጉያህ እንዳልወጣ ደጋግፈህ ያዘኝ

4. በዓለም ብልጭልጭ
ምናልባት ለጊዜው እጠቀም ይሆናል
እኔ መግዛት ስችል በሱስ ተጠምጄ ይሆናል
ይህ ሁሉ አላፊ ግን ትምክህት አይሆነኝም
አምላኬ ወደ አንተ አያጠጋጋኝም /2/

መንገዴን እንዳልስት ጌታዬ ሆይ
በትዕግስት ልጠብቅ አባቴ ሆይ /2/
ለሥጋዬ ምቾት ጌታ ሆይ
ጉዞዬን እንዳልተው ጠብቀኝ
ከጉያህ እንዳልወጣ ደጋግፈህ ያዘኝ

የትንሳኤ
Amharic
St.Gabriel

Leave a Comment

Scroll to Top