ምላሹ ምንድን ነው አንተ ላረክልኝ
ሁሉም አለህና የምሰጥህ የለኝ
ግን ያለኝን ልስጥህ አንተ የምትፈልገው
በልቤ ውስጥ ያለው ሁሌ ምስጋና ነው
ትልቅ ነው ውለታህ ቁስልህ ፈውሶኛል
ሐጥያቴን ከላዬ ፍፁም እርቆልኛል .. አቤት
ምን ብዬ ላመስግን ለታላቁ ስምህ
ደዌዬን ተቀበልክ ህመሜንም ታመህ
ከሰይጣን ባርነት እስር ልታወጣኝ
ዝቅ ብለህ መጣህ እኔን ልታድነኝ …. አቤት
እንዴት ብዬ ልግለፅ ላንተ ምስጋናዬን
ይቅርልህ ያልከኝ የዘለአለም ሞቴን
በነፃነት ልኖር ነፃ አወጣኸኝ
ህይወት አንት እንደሆክ መንገድ አሳየኸኝ …. አቤት
ታንስብህ ይሆንወይ ምስጋና የማቀርባት
ከጭንቅ ያወጣኸኝ ከዘለአለም እሳት
መንፈስህን ሳትቆጥብ ለእኔ ሰጠኸኝ
ድካሜን አንዲያግዝ ዳግም እንዲያፅናናኝ…. አቤት
እንዴት ባለው ቃል ነው ምስጋና የሚደርስህ
ለፍፁም ፍቅርህ ለታላቅ ስጦታህ
