1. የምስጋና መዝሙር ለአንተ እቀኛለሁ
በሆነው ባልሆነው መጨነቅ እተዋለሁ
የክብርህን ፀዳል አጥብቄ እሻለሁ
ተስፋዬን በሙሉ በአንተ አደርጋለሁ
የመዳኔ ምክንያት መሆንክን አውቃለሁ /2/
ምስጋናዬ ይኸው ለአንተ ምስጋናዬ
ዝማሬዬ ይኸው ለአንተ ዝማሬዬ
ውዳሴዬ ይኸው ለአንተ ውዳሴዬ
እልልታዬ ይኸው ለአንተ እልልታዬ
2. አስደናቂ ነገር አድርገህልኛል
አባትም ሳይኖረኝ አባት ሆነኸኛል
ሃዘኔንም ሽረህ ደስታ ሰጥተኸኛል
የጥርጊያውን መንገድ በስምህ አቅንተሀል
የሰይጣኑን ዱካ ከኔ አስወግደሀል /2/
ምስጋናዬ ይኸው ለአንተ ምስጋናዬ
ዝማሬዬ ይኸው ለአንተ ዝማሬዬ
ውዳሴዬ ይኸው ለአንተ ውዳሴዬ
እልልታዬ ይኸው ለአንተ እልልታዬ
3. ቃልህን ሰምቼ በኑሮዬ እንድተጋ
በደምህ ዋጀኸኝ ነፃነት ፍለጋ
ሕይወቴ እርካታ ምስጋና ታብዛልህ
ለእኔ ያደረከው ብዙ ውለታ አለህ
ለእኔ ያደረከው ብዙ ስጦታ አለህ /2/
ምስጋናዬ ይኸው ለአንተ ምስጋናዬ
ዝማሬዬ ይኸው ለአንተ ዝማሬዬ
ውዳሴዬ ይኸው ለአንተ ውዳሴዬ
እልልታዬ ይኸው ለአንተ እልልታዬ
4. ጥንትም ትሰራለህ ዛሬም ገናና ነህ
ቀድሞም እንዳየኸኝ ዛሬም ታየኛለህ
ሕይወቴ እርካታ ምስጋና ታብዛልህ
ለእኔ ያደረከው ብዙ ውለታ አለህ
ለእኔ ያደረከው ብዙ ስጦታ አለህ /2/
ምስጋናዬ ይኸው ለአንተ ምስጋናዬ
ዝማሬዬ ይኸው ለአንተ ዝማሬዬ
ውዳሴዬ ይኸው ለአንተ ውዳሴዬ
እልልታዬ ይኸው ለአንተ እልልታዬ
