እግዚአብሔር ፍቅር ነው

74

የለመኑትን ሰምቶ ቶሎ የሚፈፅም
ሁሌ ሲጠሩት አንዴም የማይደክም
አልፋና ኦሜጋ አለኝ ለዘለአለም
እግዚአብሔር ፍቅር ነው /2/

ያሰብኩት አልፈጸም ሲል በስጋ ደክሜ
የሚመክረኝ አጥቼ እስከፍጻሜ
የምጨብጠውን አጥቼ ሆኜ ደካማ ከርታታ
ገንዘብና ወርቅን የማይፈልግ አገኘውሁ ጌታ/2/

ስሙን ጠርቼ ብነግረው መሆኔን ከርታታ
በፍቅር ተመልክቶ ለወጠው ሁካታን በደስታ
ከልብ ማመን ብቻ የሚፈልግ አምላካችን ነው
ካመንበት የማይከዳን አብልጦ የሚጠብቀን ነው /2/

አንዱ ልብ ሃሳብ የሚይሄድ ስለመልካም
በአምሳሉ ለተፈጠሩት ከርሱ ለራቁትም
ሰላምን ላጣ ይሰጣል እውነተኛ እረፍት
ፍቅርንም ላጣች ነፍስ ያሳያል የፍቅርን መሠረት/2/

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top