እኔ እንደወደድኳችሁ

77

ይህቺ ናት ትዛዜ እኔ እንደወደድኳችሁ
ፍጹም ተዋደዱ እርስ በርሳችሁ

እርስ በእርሳችን በፍቅር ጠንክረን
የሰይጣን ፈላጻ ምንም ሳይበግረን
የእምነትን ጋሻ በክንዳችን ይዘን
የሰማዩ ቤታችን እንገባለን

በጸሎት በርትተን በጽናት ተጋድለን
የፍቅርን ካባ በላያችን ደርበን
እርስ በእርሳችን በአንድነት ተሳስረን
ከኃጥያት ባርነት ዛሬ እናመልጣለን

ባምላካችን ቃሉ በተስፋው ተማምነን
የሰይጣንን ስራ በፍቅር ኣሸንፈን
ልዩነታችንን ለአገልግሎት ኣድርገን
በፍቅር እራሳችንን አንድ እናደርጋለን

የእምነትን ጨረር ነጭ ልብስን ለብሰን
የፍቅርን አክሊል ለብሰን አሸብርቀን
ላላወቁት ሁሉ ጌታን አሳውቀን
የፍቅርን ሸማ እናደምቃታለን
የፍቅርን ፀሐይ እናበራታለን

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top