ከአፌ አውጥቼ ሳልናገር
ይገባሃል የኔ ነገር
አንተ የልቤን ታውቃለህና
ላወያይህ ውድዬ ና
ኢየሱሴና / ውድዬ ና
የእውነት ወዳጅ አንተ ነህና
አተን ካወኩኝ ጊዜ ጀምሮ
አረፈ ልቤ በአንተ ተማምኖ
ስጋት አይገባኝ በዕድሜ ዘመኔ
አንተ ስላለህ ሁሌም ከጐኔ
የውስጤን ጭንቀት የልቤን ስጋት
ባንተ ላይ ጥዬ አገኘው እረፍት
የነገውንም አንተ ታውቃለህ
ወደር የሌለህ ለእኔ መልካም ነህ
ታማኝ ጓደኛ ሚሰጥረኛዬ
ሁሉን የምታውቅ የልብ ጓዳዬ
ሲቃትት ውስጤ ጭንቀቴን ሰምተህ
ቶሎ በፍጥነት ከተፍ ትላለህ
