ይጣፍጥና ይመርና

100

ይጣፍጥና ይመርና
ለአንተ ይሁን ምሥጋና እንደገና
ለአንተ ይድረስ ምሥጋና እንደገና
ለአንተ ይብዛ ምሥጋና እንደገና
ለአንተ አይነስ ምሥጋና እንደገና

ብቻህን በሰማይ ሰማይህ
ሚስጥርን ገላጭ ነህ ና ካሉህ
አንዴም አትረሳ በስምህ
እግዚአግሔር ሁሉን ቻይ ጌታ ነህ
ጌታ ነህ /2/

ይኸው ምሥጋና ይብዛልህ
ይጣፍጥና ኦሆ ተመለክ በምሥጋና
ይመርና ኦሆ ተወደስ እንደገና
በሽብሸባ ኦሆ ተባረክ በምሥጋና
በእልልታ ንገስ አይበዛብህምና

እጅግ የተፈራ በጊዜው
ናቡከደነፆር ያ ጀግናው
ከምድር ወደቀ በእግርህ
ጥበብህን ኣየ በልጅህ
ጌታ ነህ /2/
ይኸው ምሥጋና ይብዛልህ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top